የማርቆስ ወንጌል (Mark)


1

1 የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ

2-3 እነሆመንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ

4 ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ

5 የይሁዳም አገር ሁሉ የኢየሩሳሌምም ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበርኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር

6 ዮሐንስም የግመል ጠጉር ለብሶ በወገቡ ጠፍር ይታጠቅ አንበጣና የበረሀ ማርም ይበላ ነበር

7 ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል

8 እኔ በውኃ አጠመቅኋችሁ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር

9 በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ

10 ወዲያውም ከውኃው በወጣ ጊዜ ሰማያት ሲቀደዱ መንፈስም እንደ ርግብ ሲወርድበት አየናየምወድህ ልጄ አንተ ነህ

11 በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ

12 ወዲያውም መንፈስ ወደ ምድረ በዳ አወጣው

13 በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ ከአራዊትም ጋር ነበረመላእክቱም አገለገሉት

14-15 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከናዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ

16 በገሊላ ባሕርም አጠገብ ሲያልፍ ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየዓሣ አጥማጆች ነበሩና

17 ኢየሱስምበኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው

18 ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት

19 ከዚያም ጥቂት እልፍ ብሎ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ደግሞ በታንኳ ላይ መረባቸውን ሲያበጁ አየ

20 ወዲያውም ጠራቸው አባታቸውንም ዘብዴዎስን ከሞያተኞቹ ጋር በታንኳ ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ

21 ወደ ቅፍርናሆምም ገቡወዲያውም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ

22 እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጻፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ

23 በዚያን ጊዜም በምኩራባቸው ርኵስ መንፈስ ያለው ሰው ነበረ

24 እርሱምየናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይከአንተ ጋር ምን አለን ? ልታጠፋን መጣህን ? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁየእግዚአብሔር ቅዱሱ ብሎ ጮኸ

25 ኢየሱስምዝም በል ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሠጸው

26 ርኵሱም መንፈስ አንፈራገጠውና በታላቅ ድምፅ ጮኾ ከእርሱ ወጣ

27 ሁሉምይህ ምንድር ነው ? በሥልጣን ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛልእነርሱም ይታዘዙለታልና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድር ነው ? ብለው እስኪጠያየቁ ድረስ አደነቁ

28 ዝናውም ወዲያው በየስፍራው ወደ ገሊላ ዙሪያ ሁሉ ወጣ

29 ወዲያውም ከምኵራብ ወጥቶ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና ወደ እንድርያስ ቤት ገባ

30 የስምዖንም አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበርስለ እርስዋም ወዲያው ነገሩት

31 ቀርቦም እጅዋን ይዞ አስነሣት ንዳዱም ወዲያው ለቀቃትና አገለገለቻቸው

32 ፀሐይም ገብቶ በመሸ ጊዜየታመሙትንና አጋንንት ያደረባቸውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ

33 ከተማይቱም ሁላ በደጅ ተሰብስባ ነበር

34 በልዩ ልዩ ደዌም የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰብዙዎችንም አጋንንት አወጣአጋንንትም ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበርና ሊናገሩ አልፈቀደላቸውም

35 ማለዳም ተነሥቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ

36 ስምዖንና ከእርሱ ጋር የነበሩትም ገሥግሠው ተከተሉት

37 ባገኙትም ጊዜሁሉ ይፈልጉሃል አሉት

38 እርሱምበዚያ ደግሞ ልሰብክ ወደ ሌላ ስፍራ በቅርብ ወዳሉ መንደሮች እንሂድ ስለዚህ ወጥቻለሁና አላቸው

39 በምኵራባቸውም እየሰበከ አጋንንትንም እያወጣ ወደ ገሊላ ሁሉ መጣ

40 ለምጻምም ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከናብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው

41 ኢየሱስም አዘነለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውናእወድዳለሁንጻ አለው

42 በተናገረም ጊዜ ለምጹ ወዲያው ለቀቀውና ነጻ

43 በብርቱም ተናግሮ ወዲያው አወጣው

44 ለማንም አንዳች እንዳትናገር ተጠንቀቅነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን አቅርብ አለው

45 እርሱ ግን ሲወጣ ብዙ ሊሰብክና ነገሩን ሊያወራ ጀመረስለዚህም ኢየሱስ ተገልጦ ወደ ከተማ መግባት ወደ ፊት ተሳነውነገር ግን በውጭ በምድረ በዳ ይኖር ነበርከየስፍራውም ወደ እርሱ ይመጡ ነበር

2

1 ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ደግሞ ገብቶ በቤት እንደ ሆነ ተሰማ

2 በደጅ ያለው ስፍራም እስኪጠባቸው ድረስ ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡቃሉንም ይነግራቸው ነበር

3 አራት ሰዎችም የተሸከሙትን ሽባ አመጡለት

4 ስለ ሕዝቡም ብዛት ወደ እርሱ ማቅረብ ቢያቅታቸው እርሱ ያለበትን የቤቱን ጣራ አነሡነድለውም ሽባው የተኛበትን አልጋ አወረዱ

5 ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውንአንተ ልጅኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው

6 ከጻፎችም አንዳንዶቹ በዚያ ተቀምጠው ነበር በልባቸውምይህ ሰው ስለ ምን እንደዚህ ያለ ስድብ ይናገራል ?

7 ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል ? ብለው አሰቡ

8 ወዲያውም ኢየሱስ በልባቸው እንዲህ እንዳሰቡ በመንፈስ አውቆ እንዲህ አላቸውበልባችሁ ይህን ስለ ምን ታስባላችሁ ?

9 ሽባውንኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስተነሣ አልጋህንም ተሸከምና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል ?

10 ነገር ግን ለሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ሊያስተሰርይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ

11 ሽባውንአንተን እልሃለሁተነሣአልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ አለው

12 ተነሥቶም ወዲያው አልጋውን ተሸክሞ በሁሉ ፊት ወጣስለዚህም ሰዎች ሁሉ ተገረሙናእንዲህ ያለ ከቶ አላየንም ብለው እግዚአብሔርን አከበሩ

13 ደግሞም በባሕር አጠገብ ወጣሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡና አስተማራቸው

14 ሲያልፍም በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረውን የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን አየናተከተለኝ አለውተነሥቶም ተከተለው

15 በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጡብዙ ነበሩ ይከተሉትም ነበር

16 ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱከቀራ ጮችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው ? አሉ

17 ኢየሱስም ሰምቶሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው

18 የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና ፈሪሳውያን ይጦሙ ነበርመጥተውምየዮሐንስና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት የሚጦሙት የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው ? አሉት

19 ኢየሱስም አላቸውሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጦሙ ይችላሉን ? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊጦሙ አይችሉም

20 ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣልበዚያ ወራትም ይጦማሉ

21 በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለምቢደረግ ግንአዲሱ መጣፊያ አሮጌውን ይቦጭቀዋልመቀደዱም የባሰ ይሆናል

22 በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለምቢደረግ ግንየወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል የወይኑም ጠጅ ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ

23 በሰንበትም በእርሻ መካከል ሲያልፍ ደቀ መዛሙርቱ እየሄዱ እሸት ይቀጥፉ ጀመር

24 ፈሪሳውያንምእነሆበሰንበት ያልተፈቀደውን ስለ ምን ያደርጋሉ ? አሉት

25 እርሱምዳዊት ባስፈለገውና በተራበ ጊዜእርሱ አብረውት ከነበሩት ጋር ያደረገውንአብያተር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ

26 ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን ? አላቸው

27 ደግሞሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም

28 እንዲሁም የሰው ልጅ ለሰንበት እንኳ ጌታዋ ነው አላቸው

3

1 ደግሞም ወደ ምኵራብ ገባበዚያም እጁ የሰለለች ሰው ነበር

2 ሊከሱትምበሰንበት ይፈውሰው እንደ ሆነ ይጠባበቁት ነበር

3 እጁ የሰለለችውንም ሰውተነሥተህ ወደ መካከል አለው

4 በሰንበት በጎ ማድረግ ተፈቅዶአልን ? ወይስ ክፉ ? ነፍስ ማዳን ወይስ መግደል ? አላቸውእነርሱም ዝም አሉ

5 ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ ዙሪያውን እየተመለከተ በቍጣ አያቸውሰውየውንምእጅህን ዘርጋ አለው

6 ዘረጋትምእጁም ዳነችፈሪሳውያንም ወጥተው ወዲያው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ከሄሮድስ ወገን ጋር ተማከሩበት

7 ኢየሱስም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ባህር ፈቀቅ አለከገሊላ የመጡም ብዙ ሰዎች ተከተሉት

8 እንዴት ትልቅ ነገርም እንዳደረገው ሰምተው ብዙ ሰዎች ከይሁዳ ከኢየሩሳሌምም ከኤዶምያስም ከዮርዳኖስ ማዶም ከጢሮስና ከሲዶና ምድርም ወደ እርሱ መጡ

9 ሰዎቹም እንዳያጋፉት ታንኳን ያቆዩለት ዘንድ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው

10 ብዙ ሰዎችን አድኖ ነበርናስለዚህም ሥቃይ ያለባቸው ሁሉ እንዲዳስሱት ይወድቁበት ነበር

11 ርኵሳን መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ተደፍተውአንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉ ጮኹ

12 እንዳይገልጡትም በጣም አዘዛቸው

13 ወደ ተራራም ወጣራሱም የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራወደ እርሱም ሄዱ

14 ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው

15 ድውዮችንም ሊፈውሱ አጋንንትንም ሊያወጡ ሥልጣን ይሆንላቸው ዘንድ አሥራ ሁለት አደረገ

16 ስምዖንንም ጴጥሮስ ብሎ ሰየመው

17 የዘብዴዎስንም ልጅ ያዕቆብን የያዕቆብንም ወንድም ዮሐንስን ቦአኔርጌስ ብሎ ሰየማቸውየነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው

18 እንድርያስንም ፊልጶስንም በርተሎሜውስንም ማቴዎስንም ቶማስንም የእልፍዮስን ልጅ ያዕቆብንም ታዴዎስንም ቀነናዊውንም ስምዖንን

19 አሳልፎ የሰጠውንም የአስቆሮቱን ይሁዳን

20 ወደ ቤትም መጡእንጀራም መብላት ስንኳ እስኪሳናቸው ድረስ እንደ ገና ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ

21 ዘመዶቹም ሰምተውአበደ ብለዋልና ሊይዙት ወጡ

22 ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችምብዔል ዜቡል አለበትደግሞበአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል ብለው ተናገሩ

23 እነርሱንም ወደ እርሱ ጠርቶ በምሳሌ አላቸውሰይጣን ሰይጣንን ሊያወጣው እንዴት ይችላል ?

24 መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም

25 ቤትም እርስ በርሱ ከተለያየ ቤት ሊቆም አይችልም

26 ሰይጣንም ራሱን ተቃውሞ ከተለያየመጨረሻ ይሆንበታል እንጂ ሊቆም አይችልም

27 ነገር ግን አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለምከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል

28 እውነት እላችኋለሁለሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል

29 በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኃጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም

30 ርኵስ መንፈስ አለበት ይሉ ነበርና

31 እናቱና ወንድሞቹም መጡ በውጭም ቆመው ወደ እርሱ ልከው አስጠሩት

32 ብዙ ሰዎችም በዙሪያው ተቀምጠው ነበሩናእነሆእናትህ ወንድሞችህም በውጭ ቆመው ይፈልጉሃል አሉት

33 መልሶምእናቴ ማን ናት ? ወንድሞቼስ እነ ማን ናቸው ? አላቸው

34 በዙሪያው ተቀምጠው ወደ ነበሩትም ተመለከተናእነሆ እናቴ ወንድሞቼም

35 የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉእርሱ ወንድሜ ነው እኅቴም እናቴም አለ

4

1 ደግሞም በባሕር ዳር ሊያስተምር ጀመረእጅግ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ ስለ ተሰበሰቡ እርሱ በታንኳ ገብቶ በባሕር ላይ ተቀመጠሕዝቡም ሁሉ በባሕር ዳር በምድር ላይ ነበሩ

2 በምሳሌም ብዙ ያስተምራቸው ነበርበትምህርቱም አላቸውስሙ

3-4 እነሆዘሪ ሊዘራ ወጣሲዘራም አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀና ወፎች መጥተው በሉት

5 ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀና ጥልቅ መሬት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ

6 ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገሥርም ስላልነበረው ደረቀ

7 ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀእሾህም ወጣና አነቀውፍሬም አልሰጠም

8 ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀና ወጥቶ አድጎ ፍሬ ሰጠአንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ አፈራ

9 የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ አለ

10 ብቻውንም በሆነ ጊዜበዙሪያው የነበሩት ከአሥራ ሁለቱ ጋር ስለ ምሳሌው ጠየቁት

11-12 እንዲህም አላቸውለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋልበውጭ ላሉት ግንአይተው እንዲያዩ እንዳይመለከቱምሰምተውም እንዲሰሙ እንዳያስተውሉምእንዳይመለሱ ኃጢአታቸውም እንዳይሰረይላቸው ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል

13 አላቸውምይህን ምሳሌ አታውቁምን ? እንዴትስ ምሳሌዎቹን ሁሉ ታውቃላችሁ ?

14 ዘሪው ቃሉን ይዘራልቃልም በተዘራበት በመንገድ ዳር የሆኑት እነዚህ ናቸው

15 በሰሙት ጊዜም ሰይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል

16 እንዲሁም በጭንጫ ላይ የተዘሩት እነዚህ ናቸውቃሉንም ሰምተው ወዲያው በደስታ ይቀበሉታል

17 ለጊዜውም ነው እንጂ በእነርሱ ሥር የላቸውምኋላም በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላሉ

18 በእሾህም የተዘሩት ሌሎች ናቸውቃሉን የሰሙት እነዚህ ናቸው

19 የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉየማያፈራም ይሆናል

20 በመልካምም መሬት የተዘሩት ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉት አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ ፍሬ የሚያፈሩት እነዚህ ናቸው

21 እንዲህም አላቸውመብራትን ከዕንቅብ ወይስ ከአልጋ በታች ሊያኖሩት ያመጡታልን ? በመቅረዝ ላይ ሊያኖሩት አይደለምን ?

22 እንዲገለጥ ባይሆን የተሰወረ የለምናወደ ግልጥ እንዲመጣ እንጂ የተሸሸገ የለም

23 የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ

24 አላቸውምምን እንድትሰሙ ተጠበቁበምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል ለእናንተም ይጨመርላችኋል

25 ላለው ይሰጠዋልናከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል

26 እርሱም አለበምድር ዘርን እንደሚዘራ ሰው የእግዚአብሔር መንግሥት እንደዚህ ናት ሌሊትና ቀን ይተኛልም ይነሣልም

27 እርሱም እንዴት እንደሚሆን ሳያውቅ ዘሩ ይበቅላል ያድግማል

28 ምድሪቱም አውቃ በመጀመሪያ ቡቃያ ኋላም ዛላ ኋላም በዛላው ፍጹም ሰብል ታፈራለች

29 ፍሬ ግን ሲበስል መከር ደርሶአልና ወዲያው ማጭድ ይልካል

30 እርሱም አለየእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እናስመስላታለን ? ወይስ በምን ምሳሌ እንመስላታለን ?

31 እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት ናትእርስዋም በምድር በተዘራች ጊዜ በምድር ካለ ዘር ሁሉ ታንሳለችበተዘራችም ጊዜ ትወጣለች ከአትክልትም ሁሉ የምትበልጥ ትሆናለች

32 የሰማይ ወፎችም በጥላዋ ሊሰፍሩ እስኪችሉ ታላላቅ ቅርንጫፎች ታደርጋለች

33 መስማትም በሚችሉበት መጠን እነዚህን በሚመስል በብዙ ምሳሌ ቃሉን ይነግራቸው ነበርያለ ምሳሌ ግን አልነገራቸውም

34 ለብቻቸውም ሲሆኑ ነገሩን ሁሉ ለገዛ ደቀ መዛሙርቱ ይፈታላቸው ነበር

35 በዚያም ቀን በመሸ ጊዜወደ ማዶ እንሻገር አላቸው

36 ሕዝቡንም ትተው በታንኳ እንዲያው ወሰዱትሌሎች ታንኳዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ

37 ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውኃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር

38 እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበርአንቅተውምመምህር ሆይስንጠፋ አይገድህምን ? አሉት

39 ነቅቶም ነፋሱን ገሠጸው ባሕሩንምዝም በልፀጥ በል አለውነፋሱም ተወ ታላቅ ፀጥታም ሆነ

40 እንዲህ የምትፈሩ ስለ ምን ነው ? እንዴትስ እምነት የላችሁም ? አላቸው

41 እጅግም ፈሩናእንግዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው ? ተባባሉ

5

1 ወደ ባሕር ማዶም ወደ ጌርጌሴኖን አገር መጡ

2 ከታንኳይቱም በወጣ ጊዜርኵስ መንፈስ የያዘው ሰው ከመቃብር ወጥቶ ወዲያው ተገናኘው

3 እርሱም በመቃብር ይኖር ነበርበሰንሰለትም ስንኳ ማንም ሊያስረው በዚያን ጊዜ አይችልም ነበር

4 ብዙ ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር ነበርና ዳሩ ግን ሰንሰለቱን ይበጣጥስ እግር ብረቱንም ይሰባብር ነበርሊያሸንፈውም የሚችል አልነበረም

5 ሁልጊዜም ሌሊትና ቀን በመቃብርና በተራራ ሆኖ ይጮኽ ነበር ሰውነቱንም በድንጋይ ይቧጭር ነበር

6 ኢየሱስንም ከሩቅ ባየ ጊዜ ሮጦ ሰገደለት

7 በታላቅ ድምፅም እየጮኸየልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይከአንተ ጋር ምን አለኝ ? እንዳታሠቃየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ አለ

8 አንተ ርኵስ መንፈስከዚህ ሰው ውጣ ብሎት ነበርና

9 ስምህ ማን ነው ? ብሎ ጠየቀውብዙዎች ነንና ስሜ ሌጌዎን ነው አለው

10 ከአገርም ውጭ እንዳይሰዳቸው አጥብቆ ለመነው

11 በዚያም በተራራ ጥግ ብዙ የእሪያ መንጋ ይሰማራ ነበርና

12 ወደ እሪያዎቹ እንድንገባ ስደደን ብለው ለመኑት

13 ኢየሱስም ፈቀደላቸውርኵሳን መናፍስቱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ገቡሁለት ሺህም የሚያህል መንጋ ከአፋፉ ወደ ባሕር ተጣደፉና በባሕር ሰጠሙ

ፍ1 ሌጌዎን ማለት ጭፍራ ማለት ነው

14 እረኞቹም ሸሽተው በከተማውና በአገሩ አወሩነገሩም ምን እንደ ሆነ ለማየት መጡ

15 ወደ ኢየሱስም መጡአጋንንትም ያደሩበትን ሌጌዎንም የነበረበትን ሰው ተቀምጦ ለብሶም ልቡም ተመልሶ አዩና ፈሩ

16 ያዩት ሰዎችም አጋንንት ላደሩበት ሰው የሆነውንና ስለ እሪያዎቹ ተረኩላቸው

17 ከአገራቸውም እንዲሄድላቸው ይለምኑት ጀመር

18 ወደ ታንኳይቱም በገባ ጊዜ አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው ከእርሱ ጋር እንዲኖር ለመነው

19 ኢየሱስም አልፈቀደለትምነገር ግንወደ ቤትህ በቤተ ሰዎችህ ዘንድ ሄደህ ጌታ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገልህ እንዴትስ እንደ ማረህ አውራላቸው አለው

20 ሄዶም ኢየሱስ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት አሥር ከተማ በሚባል አገር ይሰብክ ጀመርሁሉም ተደነቁ

21 ኢየሱስም ደግሞ በታንኳይቱ ወደ ማዶ ከተሻገረ በኋላ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡበባሕርም አጠገብ ነበረ

22 ኢያኢሮስ የተባለ ከምኵራብ አለቆች አንዱ መጣባየውም ጊዜ በእግሩ ላይ ወደቀና

23 ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት ብሎ አጥብቆ ለመነው

24 ከእርሱም ጋር ሄደብዙ ሕዝብም ተከተሉት አጋፉትም

25 ከአሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች

26 ከብዙ ባለ መድኃኒቶችም ብዙ ተሠቃየችገንዘብዋንም ሁሉ ከስራ ባሰባት እንጂ ምንም አልተጠቀመችም

27 የኢየሱስንም ወሬ ሰምታ በስተኋላው በሰዎች መካከል መጥታ ልብሱን ዳሰሰች

28 ልብሱን ብቻ የዳሰስሁ እንደ ሆነ እድናለሁ ብላለችና

29 ወዲያውም የደምዋ ምንጭ ደረቀ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች

30 ወዲያውም ኢየሱስ ከእርሱ ኃይል እንደ ወጣ በገዛ ራሱ አውቆ በሕዝቡ መካከል ዘወር ብሎልብሴን የዳሰሰ ማን ነው ? አለ

31 ደቀ መዛሙርቱምሕዝቡ ሲያጋፉህ እያየህማን ዳሰሰኝ ትላለህን ? አሉት

32 ይህንም ያደረገችውን ለማየት ዘወር ብሎ ይመለከት ነበር

33 ሴቲቱ ግን የተደረገላትን ስላወቀችእየፈራች እየተንቀጠቀጠችምመጥታ በፊቱ ተደፋች እውነቱንም ሁሉ ነገረችው

34 እርሱምልጄ ሆይእምነትሽ አድኖሻልበሰላም ሂጂ ከሥቃይሽም ተፈወሽ አላት

35 እርሱም ገና ሲናገር ከምኵራብ አለቃው ቤት ዘንድ የመጡትልጅህ ሞታለችስለ ምን መምህሩን አሁን ታደክመዋለህ ? አሉት

36 ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ቃል አድምጦ ለምኵራቡ አለቃእመን ብቻ እንጂ አትፍራ አለው

37 ከጴጥሮስም ከያዕቆብም ከያዕቆብም ወንድም ከዮሐንስ በቀር ማንም እንዲከተለው አልፈቀደም

38 ወደ ምኵራቡ አለቃ ቤትም መጥቶ ሰዎች ሲንጫጩና ሲያለቅሱ ዋይታም ሲያበዙ አየ

39 ገብቶምስለ ምን ትንጫጫላችሁ ታለቅሳላችሁም ? ብላቴናይቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም አላቸው

40 በጣምም ሳቁበትእርሱ ግን ሁሉን አስወጥቶ የብላቴናይቱን አባትና እናትም ከእርሱ ጋር የነበሩትንም ይዞ ብላቴናይቱ ወዳለችበት ገባ

41 የብላቴናይቱንም እጅ ይዞጣሊታ ቁሚ አላትፍችውም አንቺ ብላቴና ተነሽ እልሻለሁ ነው

42 ብላቴናይቱም የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረችና ወዲያው ቆማ ተመላለሰችወዲያውም ታላቅ መገረም ተገረሙ

43 ይህንም ማንም እንዳያውቅ አጥብቆ አዞአቸውየምትበላውን ስጡአት አላቸው

6

1 ከዚያም ወጥቶ ወደ ገዛ አገሩ መጣ ደቀ መዛሙርቱም ተከተሉት

2 ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመርብዙዎችም ሰምተው ተገረሙናእነዚህን ነገሮች ይህ ከወዴት አገኛቸው ? ለዚህ የተሰጠችው ጥበብ ምንድር ናት ? በእጁም የሚደረጉ እንደነዚህ ያሉ ተአምራት ምንድር ናቸው ?

3 ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን ? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን ? አሉይሰናከሉበትም ነበር

4 ኢየሱስምነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው

5 በዚያም በጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በቀርተአምር ሊያደርግ ምንም አልቻለም

6 ስለ አለማመናቸውም ተደነቀበመንደሮችም እያስተማረ ይዞር ነበር

7 አስራ ሁለቱንም ወደ እርሱ ጠራ ሁለት ሁለቱንም ይልካቸው ጀመርበርኵሳን መናፍስትም ላይ ሥልጣን ሰጣቸው

8 ለመንገድም ከበትር በቀር እንጀራም ቢሆን ከረጢትም ቢሆን መሐለቅም በመቀነታቸው ቢሆን እንዳይዙ አዘዛቸው

9 በእግራችሁ ጫማ አድርጉ እንጂ ሁለት እጀ ጠባብ አትልበሱ አለ

10 በማናቸውም ስፍራ ወደ ቤት ብትገቡ ከዚያ እስክትወጡ ድረስ በዚያው ተቀመጡ

11 ከማይቀበሉአችሁና ከማይሰሙአችሁ ስፍራ ሁሉከዚያ ወጥታችሁ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ ከእግራችሁ በታች ያለውን ትቢያ አራግፉእውነት እላችኋለሁከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ በፍርድ ቀን ይቀልላቸዋል አላቸው

12 ወጥተውም ንስሐ እንዲገቡ ሰበኩብዙ አጋንንትንም አወጡ

13 ብዙ ድውዮችንም ዘይት እየቀቡ ፈወሱአቸው

14 ስሙም ተገልጦአልና ንጉሡ ሄሮድስ በሰማ ጊዜመጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቶአል ስለዚህም ኃይል በእርሱ ይደረጋል አለ

15 ሌሎችምኤልያስ ነው አሉሌሎችምከነቢያት እንደ አንዱ ነቢይ ነው አሉ

16 ሄሮድስ ግን ሰምቶእኔ ራሱን ያስቈረጥሁት ዮሐንስ ይህ ነው እርሱ ከሙታን ተነሥቶአል አለ

17 ሄሮድስ የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን አግብቶ ነበርና በእርስዋ ምክንያት ራሱ ልኮ ዮሐንስን አስይዞ በወኅኒ አሳስሮት ነበር

18 ዮሐንስ ሄሮድስንየወንድምህ ሚስት ለአንተ ልትሆን አልተፈቀደም ይለው ነበርና

19 ሄሮድያዳ ግን ተቃውማው ልትገድለው ትፈልግ ነበር አልቻለችም

20 ሄሮድስ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው እንደ ሆነ አውቆ ይፈራውና ይጠባበቀው ነበርእርሱንም ሰምቶ በብዙ ነገር ያመነታ ነበር

21 በደስታም ይሰማው ነበርሄሮድስም በተወለደበት ቀን ለመኳንንቱና ለሻለቆቹ ለገሊላም ሹማምንት ግብር ባደረገ ጊዜ ምቹ ቀን ሆነላትና

22 የሄሮድያዳ ልጅ ገብታ ስትዘፍን ሄሮድስንና ከእርሱ ጋር የተቀመጡትን ደስ አሰኘቻቸውንጉሡም ብላቴናይቱንየምትወጂውን ሁሉ ለምኚኝ እሰጥሽማለሁ አላት

23 የመንግሥቴ እኩሌታ ስንኳ ቢሆን የምትለምኚውን ሁሉ እሰጥሻለሁ ብሎ ማለላት

24 ወጥታም ለእናትዋምን ልለምነው ? አለችእርስዋምየመጥምቁን የዮሐንስን ራስ አለች

25 ወዲያውም ፈጥና ወደ ንጉሡ ገብታየመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን ልትሰጠኝ እወዳለሁ ብላ ለመነችው

26 ንጉሡም እጅግ አዝኖ ስለ መሐላው ከእርሱም ጋር ስለ ተቀመጡት ሊነሣት አልወደደም

27 ወዲያውም ንጉሡ ባለ ወግ ልኮ ራሱን እንዲያመጣ አዘዘውሄዶም በወኅኒ ራሱን ቈረጠ

28 ራሱንም በወጭት አምጥቶ ለብላቴናይቱ ሰጣትብላቴናይቱም ለእናትዋ ሰጠች

29 ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው መጡ በድኑንም ወስደው ቀበሩት

30 ሐዋርያትም ወደ ኢየሱስ ተሰብስበው ያደረጉትንና ያስተማሩትን ሁሉ ነገሩት

31 እናንት ራሳችሁ ብቻችሁን ወደ ምድረ በዳ ኑና ጥቂት ዕረፉ አላቸውየሚመጡና የሚሄዱ ብዙዎች ነበሩናለመብላት እንኳ ጊዜ አጡ

32 በታንኳውም ብቻቸውን ወደ ምድረ በዳ ሄዱ

33 ሰዎችም ሲሄዱ አዩአቸው ብዙዎችም አወቁአቸውና ከከተሞች ሁሉ በእግር እየሮጡ ወዲያ ቀደሙአቸው ወደ እርሱም ተሰበሰቡ

34 ኢየሱስም ወጥቶ ብዙ ሕዝብ አየና እረኛ እንደሌላቸው በጎች ስለ ነበሩ አዘነላቸውብዙም ነገር ያስተምራቸው ጀመር

35 በዚያን ጊዜም ብዙ ሰዓት ካለፈ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበውቦታው ምድረ በዳ ነው አሁንም መሽቶአል

36 የሚበሉት የላቸውምና በዙሪያ ወዳሉ ገጠሮችና መንደሮች ሄደው እንጀራ ለራሳቸው እንዲገዙ አሰናብታቸው አሉት

37 እርሱ ግን መልሶእናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው አላቸውሄደን እንጀራ በሁለት መቶ ዲናር እንግዛላቸውን ? እንዲበሉም እንስጣቸውን ? አሉት

38 እርሱምስንት እንጀራ አላችሁ ? ሂዱና እዩ አላቸውባወቁም ጊዜአምስትሁለትም ዓሣ አሉት

39 ሁሉንም በየክፍሉ በለመለመ ሣር ላይ እንዲያስቀምጡአቸው አዘዛቸው

40 መቶ መቶውና አምሳ አምሳው እየሆኑ በተራ በተራ ተቀመጡ

41 አምስቱንም እንጀራ ሁለቱንም ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከእንጀራውንም ቈርሶ እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ

42 ሁለቱን ዓሣ ደግሞ ለሁሉ ከፈለሁሉም በልተው ጠገቡ

43 ከቍርስራሹም አሥራ ሁለት መሶብ የሞላ አነሡ ከዓሣውም ደግሞ

44 እንጀራውንም የበሉት ወንዶቹ አምስት ሺህ ነበሩ

45 ወዲያውም ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በታንኳ ገብተው ወደ ማዶ ወደ ቤተ ሳይዳ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው

46 ካሰናበታቸውም በኋላ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ

47 በመሸም ጊዜ ታንኳይቱ በባሕር መካከል ሳለች እርሱ ብቻውን በምድር ላይ ነበረ

48 ነፋስ ወደ ፊታቸው ነበረና እየቀዘፉ ሲጨነቁ አይቶከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣሊያልፋቸውም ይወድ ነበር

49 እነርሱ ግን በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ምትሀት መሰላቸውና ጮኹ

50 ሁሉ አይተውታልናታወኩምወዲያውም ተናገራቸውናአይዞአችሁእኔ ነኝአትፍሩ አላቸው

51 ወደ እነርሱም ወደ ታንኳይቱ ገባነፋሱም ተወበራሳቸውም ያለ መጠን እጅግ ተገረሙ

52 ስለ እንጀራው አላስተዋሉምናነገር ግን ልባቸው ደንዝዞ ነበር

53 ተሻግረውም ወደ ምድር ወደ ጌንሴሬጥ ደረሱ ታንኳይቱንም አስጠጉ

54 ከታንኳይቱም ሲወጡ ወዲያው አውቀውት

55 በዚያች አገር ሁሉ ዙሪያ ሮጡና እርሱ እንዳለ ወደ ሰሙበት ስፍራ ሕመምተኞችን በአልጋ ላይ ያመጡ ጀመር

56 በገባበትም ስፍራ ሁሉመንደርም ከተማም ገጠርም ቢሆንበገበያ ድውዮችን ያኖሩ ነበርየልብሱንም ጫፍ እንኳ ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ

7

1 ፈሪሳውያንና ከጻፎች ወገን ከኢየሩሳሌም የመጡትም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ

2 ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንድ በርኵስ ማለት ባልታጠበ እጅ እንጀራ ሲበሉ አዩ

3 ፈሪሳውያንና አይሁድም ሁሉ የሽማግሎችን ወግ ሲጠብቁ እጃቸውን ደኅና አድርገው ሳይታጠቡ አይበሉምና

4 ከገበያም ተመልሰው ካልታጠቡ አይበሉምጽዋንም ማድጋንም የናስ ዕቃንም አልጋንም እንደ ማጠብ ሌላ ነገር ሊጠብቁት የተቀበሉት ብዙ አለ

5 ፈሪሳውያንም ጻፎችምደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ወግ ስለ ምን አይሄዱም ? ነገር ግን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ይበላሉ ብለው ጠየቁት

6 እርሱ ግን እንዲህ አላቸውኢሳይያስ ስለ እናንተ ስለ ግብዞችይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው

7 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ

8 የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ

9 እንዲህም አላቸውወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል

10 ሙሴአባትህንና እናትህን አክብርደግሞአባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና

11 እናንተ ግን ትላላችሁሰው አባቱን ወይም እናቱንከእኔ የምትጠቀምበት ነገር ሁሉ ቍርባን ማለት መባ ነው ቢል

12 ለአባቱና ለእናቱ ምንም እንኳ ሊያደርግ ወደ ፊት አትፈቅዱለትም

13 ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁእንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ

14 ደግሞም ሕዝቡን ጠርቶሁላችሁ እኔን ስሙ አስተውሉም

15 ከሰው የሚወጡት ሰውን የሚያረክሱ ናቸው እንጂ ከሰው ውጭ የሚገባውስ ሊያረክሰው የሚችል ምንም የለም

16 የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ አላቸው

17 ከሕዝቡ ዘንድ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ምሳሌውን ጠየቁት

18 እርሱምእናንተ ደግሞ እንደዚህ የማታስተውሉ ናችሁን ? ከውጭ ወደ ሰው የሚገባ ሊያረክሰው ምንም እንዳይችል አትመለከቱምን ?

19 ወደ ሆድ ገብቶ ወደ እዳሪ ይወጣል እንጂ ወደ ልብ አይገባምናመብልን ሁሉ እያጠራ አላቸው

20 እርሱም አለከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ነው

21 ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ

22 ዝሙትመስረቅመግደልምንዝርነትመጐምጀትክፋትተንኰልመዳራትምቀኝነትስድብትዕቢትስንፍና ናቸውና

23 ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል

24 ከዚያም ተነሥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደወደ ቤትም ገብቶ ማንም እንዳያውቅበት ወደደ ሊሰወርም አልተቻለውም

25 ወዲያው ግን ታናሺቱ ልጅዋ ርኵስ መንፈስ ያደረባት አንዲት ሴት ስለ እርሱ ሰምታ መጣችና በእግሩ ላይ ተደፋች

26 ሴቲቱም ግሪክትውልድዋም ሲሮፊኒቃዊት ነበረችከልጅዋ ጋኔን ያወጣላት ዘንድ ለመነችው

27 ኢየሱስ ግንልጆቹ በፊት ይጠግቡ ዘንድ ተዪ የልጆቹን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባምናአላት

28 እርስዋም መልሳአዎንጌታ ሆይቡችሎች እንኳ ከማዕድ በታች ሆነው የልጆችን ፍርፋሪ ይበላሉ አለችው

29 እርሱምስለዚህ ቃልሽ ሂጂ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቶአል አላት

30 ወደ ቤትዋም ሄዳ ጋኔኑ ወጥቶ ልጅዋም በአልጋ ላይ ተኝታ አገኘች

31 ደግሞም ከጢሮስ አገር ወጥቶ በሲዶና አልፎ አሥር ከተማ በሚባል አገር መካከል ወደ ገሊላ ባሕር መጣ

32 ደንቆሮና ኰልታፋም የሆነ ሰው ወደ እርሱ አመጡ

33 እጁንም ይጭንበት ዘንድ ለመኑትከሕዝቡም ለይቶ ለብቻው ወሰደውጣቶቹንም በጆሮቹ አገባ እንትፍም ብሎ መላሱን ዳሰሰ

34 ወደ ሰማይም አሻቅቦ አይቶ ቃተተናኤፍታህ አለውእርሱም ተከፈት ማለት ነው

35 ወዲያውም ጆሮቹ ተከፈቱ የመላሱም እስራት ተፈታ አጥርቶም ተናገረ

36 ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው እነርሱ ግን ባዘዛቸውም መጠን ይልቅ እጅግ አወሩት

37 ያለ መጠንም ተገረሙናሁሉን ደኅና አድርጎአልደንቆሮችም እንዲሰሙ ዲዳዎችም እንዲናገሩ ያደርጋል አሉ

8

1 በዚያ ወራት ደግሞ ብዙ ሕዝብ ነበረ የሚበሉትም ስለሌላቸው ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ

2 ሕዝቡ ከእኔ ጋር እስካሁን ሦስት ቀን ውለዋልና የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ

3 ከእነርሱም አንዳንዶቹ ከሩቅ መጥተዋልና ጦማቸውን ወደ ቤታቸው ባሰናብታቸው በመንገድ ይዝላሉ አላቸው

4 ደቀ መዛሙርቱምበዚህ በምድረ በዳ እንጀራ ከየት አግኝቶ ሰው እነዚህን ማጥገብ ይችላል ? ብለው መለሱለት

5 እርሱምስንት እንጀራ አላችሁ ? ብሎ ጠየቃቸውእነርሱምሰባት አሉት

6 ሕዝቡም በምድር እንዲቀመጡ አዘዘሰባቱንም እንጀራ ይዞ አመሰገነቈርሶም እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠለሕዝቡም አቀረቡ

7 ጥቂትም ትንሽ ዓሣ ነበራቸውባረከውም ይህንም ደግሞ እንዲያቀርቡላቸው አዘዘ

8 በሉም ጠገቡምየተረፈውንም ቍርስራሽ ሰባት ቅርጫት አነሡ

9 የበሉትም አራት ሺህ ያህል ነበሩ

10 አሰናበታቸውምወዲያውም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ ዳልማኑታ አገር መጣ

11 ፈሪሳውያንም ወጡና ሊፈትኑት ከሰማይ ምልክት ከእርሱ ፈልገው ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ጀመር

12 በመንፈሱም እጅግ ቃተተናይህ ትውልድ ስለ ምን ምልክት ይፈልጋል ? እውነት እላችኋለሁለዚህ ትውልድ ምልክት አይሰጠውም አለ

13 ትቶአቸውም እንደ ገና ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ ማዶ ሄደ

14 እንጀራ መያዝም ረሱለእነርሱም ከአንድ እንጀራ በቀር በታንኳይቱ አልነበራቸውም

15 እርሱምተጠንቀቁከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ እርሾ ተጠበቁ ብሎ አዘዛቸው

16 እርስ በርሳቸውምእንጀራ ስለሌለን ይሆናል ብለው ተነጋገሩ

17 ኢየሱስም አውቆ እንዲህ አላቸውእንጀራ ስለሌላችሁ ስለ ምን ትነጋገራላችሁ ? ገና አልተመለከታችሁምን ? አላስተዋላችሁምን ?

18 ልባችሁስ ደንዝዞአልን ? ዓይን ሳላችሁ አታዩምን ? ጆሮስ ሳላችሁ አትሰሙምን ? ትዝስ አይላችሁምን ?

19 አምስቱን እንጀራ ለአምስት ሺህ በቈረስሁ ጊዜቍርስራሹ የሞላ ስንት መሶብ አነሣችሁ ? እነርሱምአሥራ ሁለት አሉት

20 ሰባቱን እንጀራስ ለአራት ሺህ በቈረስሁ ጊዜቍርስራሹ የሞላ ስንት ቅርጫት አነሣችሁ ? እነርሱምሰባት አሉት

21 ገና አላስተዋላችሁምን ? አላቸው

22 ወደ ቤተ ሳይዳም መጡዕውርም አመጡለትእንዲዳስሰውም ለመኑት

23 ዕውሩንም እጁን ይዞ ከመንደር ውጭ አወጣውበዓይኑም ተፍቶበት እጁንም ጭኖበትአንዳች ታያለህን ብሎ ጠየቀው

24 አሻቅቦምሰዎች እንደ ዛፍ ሲመላለሱ አያለሁ አለ

25 ከዚህም በኋላ ደግሞ እጁን በዓይኑ ላይ ጫነበት አጥርቶም አየና ዳነም ከሩቅም ሳይቀር ሁሉን ተመለከተ

26 ወደ ቤቱም ሰደደውናወደ መንደሩ አትግባ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር አለው

27 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም በፊልጶስ ቂሣርያ ወዳሉ መንደሮች ወጡ በመንገድምሰዎች እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ ? ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ጠየቃቸው

28 እነርሱምመጥምቁ ዮሐንስሌሎችም ኤልያስሌሎችም ከነቢያት አንዱ ብለው ነገሩት

29 እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ ? ብሎ ጠየቃቸውጴጥሮስምአንተ ክርስቶስ ነህ ብሎ መለሰለት

30 ስለ እርሱም ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው

31 የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበልከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣልሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመርቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር

32 ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ ይገሥጸው ጀመር

33 እርሱ ግን ዘወር አለ ደቀ መዛሙርቱንም አይቶ ጴጥሮስን ገሠጸውናወደ ኋላዬ ሂድአንተ ሰይጣንየሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር አታስብምና አለው

34 ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ እንዲህ አላቸውበኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖርራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ

35 ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልናስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል

36 ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል ?

37 ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል ?

38 በዚህም በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉየሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል

9

1 እውነት እላችኋለሁበዚህ ከቆሙት ሰዎች የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ አላቸው

2 ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸውበፊታቸውም ተለወጠልብሱም አንጸባረቀ

3 አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ

4 ኤልያስና ሙሴም ታዩአቸውከኢየሱስም ጋር ይነጋገሩ ነበር

5 ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስንመምህር ሆይበዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው

6 እጅግ ስለ ፈሩ የሚለውን አያውቅም ነበር

7 ደመናም መጥቶ ጋረዳቸውከደመናውምየምወደው ልጄ ይህ ነውእርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ

8 ድንገትም ዞረው ሲመለከቱ ከእነርሱ ጋር ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም

9 ከተራራውም ሲወርዱ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያዩትን ለማንም እንዳይነግሩ አዘዛቸው

10 ቃሉንም ይዘውከሙታን መነሣት ምንድር ነው ? እያሉ እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ

11 እነርሱምኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ እንዲገባው ጻፎች ስለ ምን ይላሉ ? ብለው ጠየቁት

12 እርሱም መልሶኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል ሁሉንም ያቀናናልስለ ሰው ልጅም እንዴት ተብሎ ተጽፎአል ? ብዙ መከራ እንዲቀበል እንዲናቅም

13 ነገር ግን እላችኋለሁኤልያስ ደግሞ መጥቶአልስለ እርሱም እንደ ተጸፈ የወደዱትን ሁሉ አደረጉበት አላቸው

14 ወደ ደቀ መዛሙርቱም በመጣ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ሲከብቡአቸው ጻፎችም ከእነርሱ ጋር ሲከራከሩ አየ

15 ወዲያውም ሕዝቡ ሁሉ ባዩት ጊዜ ደነገጡወደ እርሱም ሮጠው እጅ ነሡት

16 ጻፎችንምስለ ምን ከእነርሱ ጋር ትከራከራላችሁ ? ብሎ ጠየቃቸው

17 ከሕዝቡ አንዱ መልሶመምህር ሆይዲዳ መንፈስ ያደረበትን ልጄን ወደ አንተ አምጥቼአለሁ

18 በያዘውም ስፍራ ሁሉ ይጥለዋልአረፋም ይደፍቃልጥርሱንም ያፋጫል ይደርቃልምእንዲያወጡለትም ለደቀ መዛሙርትህ ነገርኋቸውአልቻሉምም አለው

19 እርሱም መልሶየማታምን ትውልድ ሆይእስከመቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ ? ወደ እኔ አምጡት አላቸው

20 ወደ እርሱም አመጡትእርሱንም ባየ ጊዜ መንፈስ ወዲያው አንፈራገጠውወደ ምድርም ወድቆ አረፋ እየደፈቀ ተንፈራፈረ

21 አባቱንምይህ ከያዘው ስንት ዘመን ነው ? ብሎ ጠየቀውእርሱምከሕፃንነቱ ጀምሮ ነው

22 ብዙ ጊዜም ሊያጠፋው ወደ እሳትም ወደ ውኃም ጣለውቢቻልህ ግን እዘንልን እርዳንም አለው

23 ኢየሱስምቢቻልህ ትላለህለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው

24 ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾአምናለሁአለማመኔን እርዳው አለ

25 ኢየሱስም ሕዝቡ እንደ ገና ሲራወጥ አይቶ ርኵሱን መንፈስ ገሠጸናአንተ ዲዳ ደንቆሮም መንፈስእኔ አዝሃለሁከእርሱ ውጣ እንግዲህም አትግባበት አለው

26 ጮኾም እጅግም አንፈራግጦት ወጣብዙዎችምሞተ እስኪሉ ድረስ እንደ ሙት ሆነ

27 ኢየሱስ ግን እጁን ይዞ አስነሣው ቆመም

28 ወደ ቤትም ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱእኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምንድር ነው ? ብለው ብቻውን ጠየቁት

29 ይህ ወገን በጸሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም አላቸው

30-31 ከዚያም ወጥተው በገሊላ በኩል አለፉደቀ መዛሙርቱንም ያስተምር ስለ ነበር ማንም ያውቅ ዘንድ አልወደደምለእነርሱምየሰው ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጣልይገድሉትማልተገድሎም በሦስተኛው ቀን ይነሣል ይላቸው ነበር

32 እነርሱም ነገሩን አላስተዋሉምእንዳይጠይቁትም ፈሩ

33 ወደ ቅፍርናሆምም መጣበቤትም ሆኖበመንገድ እርስ በርሳችሁ ምን ተነጋገራችሁ ? ብሎ ጠየቃቸው

34 እነርሱ ግን በመንገድከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን ? ተባብለው ነበርና ዝም አሉ

35 ተቀምጦም አሥራ ሁለቱን ጠርቶሰው ፊተኛ ሊሆን ቢወድ ከሁሉ በኋላ የሁሉም አገልጋይ ይሁን አላቸው

36 ሕፃንም ይዞ በመካከላቸው አቆመው አቅፎም

37 እንደዚህ ካሉ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላልየሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን እንጂ እኔን አይቀበልም አላቸው

38 ዮሐንስ መልሶመምህር ሆይአንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው

39 ስለማይከተለንም ከለከልነው አለውኢየሱስ ግን አለበስሜ ተአምር ሠርቶ በቶሎ በእኔ ላይ ክፉ መናገር የሚችል ማንም የለምና አትከልክሉት

40 የማይቃወመን እርሱ ከእኛ ጋር ነውና

41 የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ ጽዋ ውኃ የሚያጠጣችሁ ሁሉዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ

42 በእኔም ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለው ነበር

43-44 እጅህ ብታሰናክልህ ቍረጣትሁለት እጅ ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመሄድ ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻላል

45-46 እግርህ ብታሰናክልህ ቍረጣትሁለት እግር ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ወደማይጠፋ እሳት ከመጣል አንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል

47-48 ዓይንህ ብታሰናክልህ አውጣትሁለት ዓይን ኖሮህ ትላቸው ወደማይሞትበት እሳቱም ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነመ እሳት ከመጣል አንዲት ዓይን ኖራህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል

49 ሰው ሁሉ በእሳት ይቀመማልናመሥዋዕትም ሁሉ በጨው ይቀመማል

50 ጨው መልካም ነውጨው ግን አልጫ ቢሆን በምን ታጣፍጡታላችሁ ? በነፍሳችሁ ጨው ይኑርባችሁእርስ በርሳችሁም ተስማሙ

10

1 ከዚያም ተነሥቶ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ይሁዳ አገር መጣደግሞም ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ እንደ ልማዱም ደግሞ ያስተምራቸው ነበር

2 ፈሪሳውያንም ቀርበውሰው ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን ? ብለው ሊፈትኑት ጠየቁት

3 እርሱ ግን መልሶሙሴ ምን አዘዛችሁ ? አላቸው

4 እነርሱምሙሴስ የፍችዋን ጽሕፈት ጽፎ እንዲፈታት ፈቀደ አሉ

5 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸውስለ ልባችሁ ጥንካሬ ይህችን ትእዛዝ ጻፈላችሁ

6 ከፍጥረት መጀመሪያ ግን እግዚአብሔር ወንድና ሴት አደረጋቸው

7 ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል

8 ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም

9 እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው

10 በቤትም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ነገር ጠየቁት

11 እርሱምሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በእርስዋ ላይ ያመነዝራል

12 እርስዋም ባልዋን ፈትታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች አላቸው

13 እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡደቀ መዛሙርቱም ያመጡአቸውን ገሠጹአቸው

14 ኢየሱስ ግን አይቶ ተቈጣናሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉ አትከልክሉአቸውየእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና

15 እውነት እላችኋለሁየእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም አላቸው

16 አቀፋቸውም እጁንም ጭኖ ባረካቸው

17 እርሱም በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተንበረከከለትናቸር መምህር ሆይየዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ ? ብሎ ጠየቀው

18 ኢየሱስምስለ ምን ቸር ትለኛለህ ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም

19 ትእዛዛትን ታውቃለህአታመንዝርአትግደልአትስረቅበሐሰት አትመስክርአታታልልአባትህንና እናትህን አክብር አለው

20 እርሱም መልሶመምህር ሆይይህን ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ አለው

21 ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውናአንድ ነገር ጐደለህሂድያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥበሰማይም መዝገብ ታገኛለህመስቀሉንም ተሸክመህ ተከተለኝ አለው

22 ነገር ግን ስለዚህ ነገር ፊቱ ጠቈረብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነም ሄደ

23 ኢየሱስም ዘወር ብሎ አይቶ ደቀ መዛሙርቱንገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል አላቸው

24 ደቀ መዛሙርቱም እነዚህን ቃሎች አደነቁኢየሱስም ደግሞ መልሶልጆች ሆይበገንዘብ ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው

25 ባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል አላቸው

26 እነርሱም ያለ መጠን ተገረሙና እርስ በርሳቸውእንግዲያ ማን ሊድን ይችላል ? ተባባሉ

27 ኢየሱስም ተመለከታቸውናይህ በእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ በሰው ዘንድ አይቻልምበእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላልና አለ

28 ጴጥሮስምእነሆእኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ይለው ጀመር

29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለእውነት እላችኋለሁስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ

30 አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን ወንድሞችንና እኅቶችንም እናቶችንም ልጆችንም እርሻንም መቶ እጥፍበሚመጣውም ዓለም የዘላለም ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም

31 ግን ብዙ ፊተኞች ኋለኞች ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ

32 ወደ ኢየሩሳሌምም ሊወጡ በመንገድ ነበሩኢየሱስም ይቀድማቸው ነበርና ተደነቁየተከተሉትም ይፈሩ ነበርደግሞም አሥራ ሁለቱን ወደ እርሱ አቅርቦ ይደርስበት ዘንድ ያለውን ይነግራቸው ጀመር

33 እነሆወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለንየሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣልየሞት ፍርድም ይፈርዱበታልለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል

34 ይዘብቱበትማል ይተፉበትማል ይገርፉትማል ይገድሉትማልበሦስተኛውም ቀን ይነሣል አላቸው

35 የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ወደ እርሱ ቀርበውመምህር ሆይየምንለምንህን ሁሉ እንድታደርግልን እንወዳለን አሉት

36 እርሱምምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ ? አላቸው

37 እነርሱምበክብርህ ጊዜ አንዳችን በቀኝ አንዳችንም በግራህ መቀመጥን ስጠን አሉት

38 ኢየሱስ ግንየምትለምኑትን አታውቁምእኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡእኔ የምጠመቀውንስ ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን ? አላቸው

39 እነርሱምእንችላለን አሉትኢየሱስምእኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁእኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ

40 በቀኝና በግራ መቀመጥ ግን ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ የምሰጥ እኔ አይደለሁም አላቸው

41 አሥሩም ሰምተው በያዕቆብና በዮሐንስ ይቈጡ ጀመር

42 ኢየሱስም ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸውየአሕዛብ አለቆች ተብሎ የምታስቡት እንዲገዙአቸው ታላላቆቻቸውም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ

43 በእናንተስ እንዲህ አይደለምነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን

44 ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የሁሉ ባሪያ ይሁን

45 እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም

46 ወደ ኢያሪኮም መጡከደቀ መዛሙርቱና ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጣ የጤሜዎስ ልጅ ዕውሩ በርጤሜዎስ እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር

47 የናዝሬቱ ኢየሱስም እንደ ሆነ በሰማ ጊዜየዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይማረኝ እያለ ይጮኽ ጀመር

48 ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹትእርሱ ግንየዳዊት ልጅ ሆይማረኝ እያለ አብዝቶ ጮኸ

49 ኢየሱስም ቆመናጥሩት አለዕውሩንምአይዞህተነሣይጠራሃል ብለው ጠሩት

50 እርሱም እየዘለለ ተነሣና ልብሱን ጥሎ ወደ ኢየሱስ መጣ

51 ኢየሱስም መልሶምን ላደርግልህ ትወዳለህ ? አለውዕውሩምመምህር ሆይአይ ዘንድ አለው

52 ኢየሱስምሂድእምነትህ አድኖሃል አለውወዲያውም አየ በመንገድም ተከተለው

11

1 ወደ ኢየሩሳሌምም ከደብረ ዘይት አጠገብ ወዳሉቱ ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ

2 በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱወዲያውም ወደ እርስዋ ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁፈትታችሁ አምጡልኝ

3 ማንምስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ? ቢላችሁለጌታ ያስፈልገዋል በሉትወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል አላቸው

4 ሄዱም ውርንጫውንም በመንገድ መተላለፊያ በደጅ ውጭ ታስሮ አገኙትፈቱትም

5 በዚያም ከቆሙት አንዳንዶቹውርንጫውን የምትፈቱት ምን ልታደርጉት ነው አሉአቸው

6 እነርሱም ኢየሱስ እንዳዘዘ አሉአቸውተዉአቸውም

7 ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡትልብሳቸውንም በላዩ ጣሉተቀመጠበትም

8 ብዙ ሰዎችም ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቈረጡ ያነጥፉ ነበር

9 የሚቀድሙትም የሚከተሉትምሆሣዕናበጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው

10 በጌታ ስም የምትመጣ የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናትሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር

11 ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደስ ገባዘወር ብሎም ሁሉን ከተመለከተ በኋላጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ ከአሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ

12 በማግሥቱም ከቢታንያ ሲወጡ ተራበ

13 ቅጠልም ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ምናልባት አንዳች ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ መጣነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና መጥቶ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም

14 መልሶምከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ አላትደቀ መዛሙርቱም ሰሙ

15 ወደ ኢየሩሳሌምም መጡወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያወጣ ጀመርየገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ

16 ዕቃም ተሸክሞ ማንም በመቅደስ ሊያልፍ አልፈቀደም

17 አስተማራቸውምቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ የተጻፈ አይደለምን ? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው

18 የካህናት አለቆችም ጻፎችም ሰምተውሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ይገረሙ ስለ ነበር ይፈሩት ነበርና እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ፈለጉ

19 ማታ ማታም ከከተማ ወደ ውጭ ይወጣ ነበር

20 ማለዳም ሲያልፉ በለሲቱን ከሥርዋ ደርቃ አዩአት

21 ጴጥሮስም ትዝ ብሎትመምህር ሆይእነሆየረገምሃት በለስ ደርቃለች አለው

22 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸውበእግዚአብሔር እመኑ

23 እውነት እላችኋለሁማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠርይህን ተራራተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል

24 ስለዚህ እላችኋለሁየጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑይሆንላችሁማል

25 ለጸሎትም በቆማችሁ ጊዜበሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁበማንም ላይ አንዳች ቢኖርባችሁ ይቅር በሉት

26 እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም

27 ደግሞም ወደ ኢየሩሳሌም መጡእርሱም በመቅደስ ሲመላለስየካህናት አለቆችና ጻፎች ሽማግሌዎችም ወደ እርሱ መጥተው

28 እነዚህን በምን ሥልጣን ታደርጋለህ ? ወይስ እነዚህን ለማድረግ ይህን ሥልጣን ማን ሰጠህ ? አሉት

29 ኢየሱስምእኔም አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁእናንተም መልሱልኝእኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ

30 የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረችን ወይስ ከሰው ? መልሱልኝ አላቸው

31 እርስ በርሳቸውም ሲነጋገሩከሰማይ ነው ብንልእንግዲያውስ ስለ ምን አላመናችሁበትም ? ይለናል

32 ነገር ግንከሰው ነው እንበልን ? አሉሁሉ ዮሐንስን በእውነት እንደ ነቢይ ያዩት ነበርና ሕዝቡን ፈሩ

33 ለኢየሱስም መልሰውአናውቅም አሉት ኢየሱስምእኔም በምን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም አላቸው

12

1 በምሳሌም ይነግራቸው ጀመርአንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለቅጥርም ቀጠረለትመጥመቂያም ማሰለትግንብም ሠራና ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ

2 በጊዜውም ከወይን አትክልት ፍሬ ከገበሬዎቹ እንዲቀበል አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎቹ ላከ

3 ይዘውም ደበደቡት ባዶውንም ሰደዱት

4 ዳግመኛም ሌላውን ባሪያ ወደ እነርሱ ላከ እርሱንም ወግረው ራሱን አቈሰሉት አዋርደውም ሰደዱት

5 ሌላውንም ላከእርሱንም ገደሉትከሌሎችም ከብዙዎች አንዳንዱን ደበደቡ አንዳንዱንም ገደሉ

6 የሚወደው አንድ ልጅ ገና ነበረውልጄንስ ያፍሩታል ብሎ እርሱን ከሁሉ በኋላ ወደ እነርሱ ላከ

7 እነዚያ ገበሬዎች ግን እርስ በርሳቸውወራሹ ይህ ነውእንግደለውርስቱም ለኛ ይሆናል ተባባሉ

8 ይዘውም ገደሉትከወይኑም አትክልት ወደ ውጭ ጣሉት

9 እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ ምን ያደርጋል ? ይመጣል ገበሬዎቹንም ያጠፋልየወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል

10-11 ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነይህም ከጌታ ዘንድ ሆነለዓይኖቻችንም ድንቅ ነውየሚለውን ይህን መጽሐፍ አላነበባችሁምን ?

12 ምሳሌውንም ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አውቀዋልና ሊይዙት ፈለጉነገር ግን ሕዝቡን ፈሩትተውትም ሄዱ

13 በንግግርም ሊያጠምዱት ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን የሆኑትን ወደ እርሱ ላኩ

14 መጥተውምመምህር ሆይየሰውን ፊት ሳትመለከት በእውነት የእግዚአብሔር መንገድ ታስተምራለህና እውነተኛ እንደ ሆንህ ለማንምም እንዳታደላ እናውቃለንለቄሣር ግብር መስጠት ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም ? እንስጥን ወይስ አንስጥ ? አሉት

15 እርሱ ግን ግብዝነታቸውን አውቆለምን ትፈትኑኛላችሁ ? አየው ዘንድ አንድ ዲናር አምጡልኝ አላቸው

16 እነርሱም አመጡለትይህች መልክ ጽሕፈቲቱስ የማን ናት ? አላቸውእነርሱምየቄሣር ናት አሉት

17 ኢየሱስም መልሶየቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ አላቸውበእርሱም ተደነቁ

18 ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጥተው ጠየቁት እንዲህም አሉት

19 መምህር ሆይሙሴየአንድ ሰው ወንድም ሚስቱን ትቶ ልጅ ሳያስቀር ቢሞትወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ ብሎ ጻፈልን

20 ሰባት ወንድማማቾች ነበሩፊተኛውም ሚስት አግብቶ ዘር ሳያስቀር ሞተ

21 ሁለተኛውም አገባትዘርም ሳይተው ሞተሦስተኛውም እንዲሁ

22 ሰባቱም አገቡአትዘርም አላስቀሩምከሁሉም በኋላ ሴቲቱ ደግሞ ሞተች

23 ሰባቱ አግብተዋታልና በትንሣኤ ቀን ሲነሡ ከእነርሱ ለማናቸው ሚስት ትሆናለች ?

24 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸውመጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ስለዚህ የምትስቱ አይደለምን ?

25 ከሙታንስ ሲነሡ በሰማያት እንዳሉ መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡምአይጋቡምም

26 ስለ ሙታን ግን እንዲነሡ እግዚአብሔርእኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቍጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን ?

27 የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለምእንግዲህ እጅግ ትስታላችሁ

28 ከጻፎችም አንዱ ቀርቦ ሲከራከሩ ሰማና መልካም አድርጎ እንደ መለሰላቸው አስተውሎከሁሉ ፊተኛይቱ ትእዛዝ ማናቸይቱ ናት ? ብሎ ጠየቀው

29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለውከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱእስራኤል ሆይስማጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው

30 አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናትፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት

31 ሁለተኛይቱምባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናትከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም

32 ጻፊውምመልካም ነውመምህር ሆይአንድ ነው ከእርሱም በቀር ሌላ የለም ብለህ በእውነት ተናገርህ

33 በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኃይልም እርሱን መውደድባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው አለው

34 ኢየሱስም በአእምሮ እንደ መለሰ አይቶአንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም አለውከዚህም በኋላ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም

35 ኢየሱስም በመቅደስ ሲያስተምር መልሶ እንዲህ አለጻፎች ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው እንዴት ይላሉ ?

36 ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስጌታ ጌታዬንጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው አለ

37 ዳዊትም ራሱ ጌታ አለውእንዴትስ ልጁ ይሆናል ? ብዙ ሕዝብም በደስታ ይሰሙት ነበር

38-39 ሲያስተምርም እንዲህ አለረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርንበገበያም ሰላምታንበምኵራብም የከበሬታን ወንበርበግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ

40 የመበለቶችን ቤት የሚበሉ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ

41 ኢየሱስም በመዝገብ አንጻር ተቀምጦ ሕዝቡ በመዝገብ ውስጥ ገንዘብ እንዴት እንዲጥሉ ያይ ነበርብዙ ባለ ጠጎችም ብዙ ይጥሉ ነበር

42 አንዲትም ድሀ መበለት መጥታ አንድ ሳንቲም የሚያህሉ ሁለት ናስ ጣለች

43 ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶእውነት እላችኋለሁበመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች

44 ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልናይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አላቸው

13

1 እርሱም ከመቅደስ ሲወጣ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱመምህር ሆይእንዴት ያሉ ድንጋይዎችና እንዴት ያሉ ሕንጻዎች እንደ ሆኑ እይ አለው

2 ኢየሱስም መልሶእነዚህን ታላላቅ ሕንጻዎች ታያለህን ? ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አለው

3 በመቅደስም ትይዩ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለጴጥሮስና ያዕቆብ ዮሐንስም እንድርያስም

4 ንገረንይህ መቼ ይሆናል ? ይህስ ሁሉ ይፈጸም ዘንድ እንዳለው ምልክቱ ምንድር ነው ? ብለው ለብቻቸው ጠየቁት

5 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ ይላቸው ጀመርማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ

6 ብዙዎችእኔ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉናብዙዎችንም ያስታሉ

7 ጦርንም የጦርንም ወሬ በሰማችሁ ጊዜ አትደንግጡይህ ሊሆን ግድ ነውናነገር ግን መጨረሻው ገና ነው

8 ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልናበልዩ ልዩ ስፍራ የምድር መናወጥ ይሆናልራብ ይሆናልእነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው

9 እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ

10 አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል

11 ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩየሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና

12 ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣልልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉይገድሉአቸውማል

13 በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁእስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል

14 ነገር ግን በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩአንባቢው ያስተውልበዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ

15 በሰገነትም ያለ ወደ ቤት አይውረድ ከቤቱም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይግባ

16 በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ

17 በዚያን ወራትም ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው

18 ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ

19 በዚያን ወራት እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያልሆነ ደግሞም የማይሆን የመከራ ዓይነት ይሆናልና

20 ጌታስ ወራቶቹን ባያሳጥርሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነምነገር ግን ስለ መረጣቸው ምርጦች ወራቶቹን አሳጠረ

21 በዚያን ጊዜም ማንምእነሆክርስቶስ ከዚህ አለወይምእነሆከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ

22 ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉናቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ

23 እናንተ ግን ተጠንቀቁእነሆአስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ

24 በዚያን ወራት ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሐይ ይጨልማል ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም

25 ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉየሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ

26 በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል

27 በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል

28 ምሳሌውንም ከበለስ ተማሩጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቈጠቍጥያን ጊዜ በጋ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ

29 እንዲሁ ደግሞ እናንተ ይህን ሁሉ መሆኑን ስታዩ ቀርቦ በደጅ እንደ ሆነ እወቁ

30 እውነት እላችኋለሁይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም

31 ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም

32 ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም

33 ጊዜው መቼ እንዲሆን አታውቁምና ተጠንቀቁትጉጸልዩም

34 ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደ ሄደ ሰው ነውለባሮቹም ሥልጣን ለእያንዳንዱም ሥራውን ሰጥቶ በረኛውን እንዲተጋ አዘዘ

35 እንግዲህ በማታ ቢሆን ወይም በእኩለ ሌሊት ወይም ዶሮ ሲጮኽ ወይም በማለዳ ቢሆን ባለቤቱ መቼ እንዲመጣ አታውቁምና

36 ድንገት መጥቶ ተኝታችሁ እንዳያገኛችሁ ስለዚህ ትጉ

37 ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁትጉ

14

1 ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረየካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር

2 የሕዝብ ሁከት እንዳይሆን በበዓል አይሁን ይሉ ነበርና

3 እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜበማዕድ ተቀምጦ ሳለአንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ ናርዶስ ሽቱ የመላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ ይዛ መጣችቢልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው

4 አንዳንዶችምይህ የሽቱ ጥፋት ለምንድር ነው ?

5 ይህ ሽቱ ከሦስት መቶ ዲናር በሚበልጥ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና ብለው በራሳቸው ይቈጡ ነበርእርስዋንም ነቀፉአት

6 ኢየሱስ ግን እንዲህ አለተዉአትስለ ምን ታደክሙአታላችሁ ? መልካም ሥራ ሠርታልኛለች

7 ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉናበማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁእኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም

8 የተቻላትን አደረገችአስቀድማ ለመቃብሬ ሥጋዬን ቀባችው

9 እውነት እላችኋለሁይህ ወንጌል በዓለሙ ሁሉ በሚሰበክበት በማናቸውም ስፍራእርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ ሊሆን ይነገራል

10 ከአሥራ ሁለቱም አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ

11 ሲሰሙም ደስ አላቸው ብርም ይሰጡት ዘንድ ተስፋ ሰጡትበሚመች ጊዜም እንዴት አድርጎ አሳልፎ እንዲሰጠው ይፈልግ ነበር

12 ፋሲካን በሚያርዱበት በቂጣ በዓል መጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ሄደን ልናሰናዳ ትወዳለህ ? አሉት

13 ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ላከ እንዲህም አላቸውወደ ከተማ ሂዱማድጋ ውኃ የተሸከመ ሰውም ይገናኛችኋል

14 ተከተሉትየሚገባበትንም የቤቱን ጌታመምህሩከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ወዴት ነው ? ይላል በሉት

15 እርሱም በደርብ ላይ ያለውን የተሰናዳና የተነጠፈ ታላቅ አዳራሽ ያሳያችኋል

16 በዚያም አሰናዱልንደቀ መዛሙርቱም ወጡ ወደ ከተማም ሄደው እንዳላቸው አገኙፋሲካንም አሰናዱ

17 በመሸም ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ጋር መጣ

18 ተቀምጠውም ሲበሉ ኢየሱስእውነት እላችኋለሁከእናንተ አንዱእርሱም ከእኔ ጋር የሚበላው አሳልፎ ይሰጠኛል አለ

19 እነርሱም ያዝኑእያንዳንዳቸውምእኔ እሆንን ? ይሉት ጀመር

20 እርሱም መልሶከአሥራ ሁለቱ አንዱ ከእኔ ጋር ወደ ወጭቱ እጁን የሚያጠልቀው ነው

21 የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳልነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር አላቸው

22 ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ሰጣቸውናእንካችሁይህ ሥጋዬ ነው አለ

23 ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸውሁሉም ከእርሱ ጠጡ

24 እርሱምይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው

25 እውነት እላችኋለሁበእግዚአብሔር መንግሥት ከወይኑ ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ደግሞ አልጠጣውም አላቸው

26 መዝሙርም ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ወጡ

27 ኢየሱስምበዚች ሌሊት ሁላችሁ በእኔ ትሰናከላላችሁእረኛዉን እመታለሁ በጎችም ይበተናሉ የሚል ተጽፎአልና

28 ነገር ግን ከተነሣሁ በኋላ ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ አላቸው

29 ጴጥሮስምሁሉም ቢሰናከሉ እኔ ግን ከቶ አልሰናከልም አለው

30 ኢየሱስምእውነት እልሃለሁዛሬ በዚች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ አለው

31 እርሱም ቃሉን አበርትቶከአንተ ጋር የምሞት እንኳ ቢሆን ከቶ አልክድህም አለሁሉም ደግሞ እንደዚሁ አሉ

32 ጌቴሴማኒ ወደምትባልም ስፍራ መጡደቀ መዛሙርቱንምስጸልይ ሳለሁበዚህ ተቀመጡ አላቸው

33 ጴጥሮስንና ያዕቆብን ዮሐንስንም ከእርሱ ጋር ወሰደሊደነግጥም ሊተክዝም ጀመረና

34 ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነችበዚህ ቈዩ ትጉም አላቸው

35 ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በምድርም ወድቆይቻልስ ቢሆን ሰዓቲቱ ከእርሱ እንድታልፍ ጸለየና

36 አባ አባት ሆይሁሉ ይቻልሃልይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ

37 መጣም ተኝተውም አገኛቸውጴጥሮስንምስምዖን ሆይተኝተሃልን ? አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን ?

38 ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ ጸልዩምመንፈስስ ተዘጋጅታለችሥጋ ግን ደካማ ነው አለው

39 ደግሞም ሄዶ ያንኑ ቃል ጸለየ

40 ደግሞም መጥቶ ዓይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸውየሚመልሱለትንም አላወቁም

41 ሦስተኛም መጥቶእንግዲህስ ተኙ ዕረፉምይበቃልሰዓቲቱ ደረሰችእነሆየሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል

42 ተነሡእንሂድእነሆአሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቦአል አላቸው

43 ወዲያውም ገና ሲናገር ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣከእርሱም ጋር ብዙ ሰዎች ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከጻፎች ከሽማግሌዎችም ዘንድ መጡ

44 አሳልፎ የሚሰጠውምየምስመው እርሱ ነውያዙት ተጠንቅቃችሁም ውሰዱት ብሎ ምልክት ሰጥቶአቸው ነበር

45 መጥቶም ወዲያው ወደ እርሱ ቀረበናመምህር ሆይመምህር ሆይብሎ ሳመው

46 እነርሱም እጃቸውን በእርሱ ላይ ጭነው ያዙት

47 በአጠገብ ከቆሙት ግን አንዱ ሰይፉን መዞ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ መታ ጆሮውንም ቈረጠ

48 ኢየሱስም መልሶወንበዴ እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁን ?

49 በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስኖር አልያዛችሁኝምነገር ግን መጻሕፍት ይፈጸሙ ዘንድ ይህ ሆነ አላቸው

50 ሁሉም ትተውት ሸሹ

51 ዕርቃኑን በነጠላ የሸፈነ አንድ ጎበዝ ይከተለው ነበር

52 ጎበዛዝቱም ያዙትእርሱ ግን ነጠላውን ትቶ ዕራቁቱን ሸሸ

53 ኢየሱስንም ወደ ሊቀ ካህናቱ ወሰዱትየካህናት አለቆችም ሁሉ ሽማግሌዎችም ጻፎችም ተሰበሰቡ

54 ጴጥሮስም እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ በሩቁ ተከተለውከሎሌዎችም ጋር ተቀምጦ እሳት ይሞቅ ነበር

55 የካህናት አለቆችም ሸንጎውም ሁሉ እንዲገድሉት በኢየሱስ ላይ ምስክር ይፈልጉ ነበርአላገኙምም

56 ብዙዎች በሐሰት ይመሰክሩበት ነበርናምስክርነታቸው ግን አልተሰማማም

57-58 ሰዎችም ተነሥተውእኔ ይህን በእጅ የተሠራውን ቤተ መቅደስ አፈርሰዋለሁ በሦስት ቀንም ሌላውን በእጅ ያልተሠራውን እሠራለሁ ሲል ሰማነው ብለው በሐሰት መሰከሩበት

59 ምስክርነታቸውም እንዲሁ እንኳ አልተሰማማም

60 ሊቀ ካህናቱም በመካከላቸው ተነሥቶአንዳች አትመልስምን ? እነዚህስ በአንተ ላይ የሚመሰክሩብህ ምንድር ነው ? ብሎ ኢየሱስን ጠየቀው

61 እርሱ ግን ዝም አለ አንዳችም አልመለሰምደግሞ ሊቀ ካህናቱ ጠየቀውናየቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን ? አለው

62 ኢየሱስምእኔ ነኝየሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ

63 ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደናከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን ምን ያስፈልገናል ?

64 ስድቡን ሰማችሁምን ይመስላችኋል ? አለእነርሱም ሁሉሞት ይገባዋል ብለው ፈረዱበት

65 አንዳንዶችም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ይጐስሙትናትንቢት ተናገር ይሉት ጀመርሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት

66 ጴጥሮስም በግቢ ውስጥ ወደ ታች ሳለ ከሊቀ ካህናቱ ገረዶች አንዲቱ መጣች

67 ጴጥሮስም እሳት ሲሞቅ አይታ ተመለከተችውናአንተ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበርህ አለችው

68 እርሱ ግንየምትዪውን አላውቅም አላስተውልምም ብሎ ካደወደ ውጭም ወደ ደጅ ወጣዶሮም ጮኸ

69 ገረዲቱም አይታው በዚያ ለቆሙትይህም ከእነርሱ ወገን ነው ስትል ሁለተኛ ትነግራቸው ጀመር

70 እርሱም ደግሞ ካደጥቂት ቈይተውም በዚያ የቆሙት ዳግመኛ ጴጥሮስንየገሊላ ሰው ነህና ከእነርሱ ወገን በእውነት ነህ አሉት

71 እርሱ ግንይህን የምትሉትን ሰው አላውቀውም ብሎ ይረገምና ይምል ጀመርወዲያውም ዶሮ ሁለተኛ ጮኸ

72 ጴጥሮስንም ኢየሱስዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው ቃል ትዝ አለውነገሩንም አስቦ አለቀሰ

15

1 ወዲያውም ማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎችና ከጻፎች ከሸንጎውም ሁሉ ጋር ከተማከሩ በኋላኢየሱስን አሳስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት

2 ጲላጦስምአንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን ? ብሎ ጠየቀውእርሱምአንተ አልህ ብሎ መለሰለት

3 የካህናት አለቆችም ብዙ ያሳጡት ነበርእርሱ ግን ምንም አልመለሰም

4 ጲላጦስም ደግሞአንዳች አትመልስምን ? እነሆበስንት ነገር ያሳጡሃል ብሎ ጠየቀው

5 ኢየሱስም ከዚያ በኋላ ጲላጦስ እስኪደነቅ ድረስ ምንም አልመለሰም

6 በዚያም በዓል የለመኑትን አንድ እስረኛ ይፈታላቸው ነበር

7 በዓመፅም ነፍስ ከገደሉት ከዓመፀኞች ጋር የታሰረ በርባን የተባለ ነበረ

8 ሕዝቡም ወጥተው እንደ ልማዱ ያደርግላቸው ዘንድ እየጮኹ ይለምኑት ጀመር

9 ጲላጦስምየአይሁድን ንጉሥ እፈታላችሁ ዘንድ ትወዳላችሁን ? ብሎ መለሰላቸው

10 የካህናት አለቆች በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና

11 የካህናት አለቆች ግን በርባንን በእርሱ ፈንታ ይፈታላቸው ዘንድ ሕዝቡን አወኩአቸው

12 ጲላጦስም ዳግመኛ መልሶእንግዲህ የአይሁድ ንጉሥ የምትሉትን ምን ላደርገው ትወዳላችሁ ? አላቸው

13 እነርሱም ዳግመኛስቀለው እያሉ ጮኹ

14 ጲላጦስምምን ነው ? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው ? አላቸውእነርሱ ግንስቀለው እያሉ ጩኸት አበዙ

15 ጲላጦስም የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታላቸውኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠ

16 ወታደሮችም ፕራይቶሪዮን ወደሚባል ግቢ ውስጥ ወሰዱትጭፍራውንም ሁሉ በአንድነት ጠሩ

17 ቀይ ልብስም አለበሱትየእሾህ አክሊልም ጎንጉነው ደፉበት

18 የአይሁድ ንጉሥ ሆይሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ እጅ ይነሱት ጀመር

19 ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትምተንበርክከውም ሰገዱለት

20 ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉትልብሱንም አለበሱትሊሰቅሉትም ወሰዱት

21 አንድ መንገድ አላፊም የአሌክስንድሮስና የሩፎስ አባት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት

22 ትርጓሜውም የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ ወሰዱት

23 ከርቤም የተቀላቀለበትን የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡትእርሱ ግን አልተቀበለም

24 ሰቀሉትምልብሱንም ማን ማን እንዲወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉ

25 በሰቀሉትም ጊዜ ሦስት ሰዓት ነበረ

26 የክሱ ጽሕፈትምየአይሁድ ንጉሥ የሚል ተጽፎ ነበር

27 ከእርሱም ጋር ሁለት ወንበዶች አንዱን በቀኙ አንዱንም በግራው ሰቀሉ

28 መጽሐፍምከአመፀኞች ጋር ተቆጠረ ያለው ተፈጸመ

29 የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡት ነበርናቤተ መቅደስን የምታፈርስ በሦስት ቀንም የምትሠራ

30 ከመስቀል ወርደህ ራስህን አድን አሉ

31 እንዲሁም የካህናት አለቆች ደግሞ ከጻፎች ጋር እርስ በርሳቸው እየተዘባበቱሌሎችን አዳነራሱን ሊያድን አይችልም

32 አይተን እናምን ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስ አሁን ከመስቀል ይውረድ አሉከእርሱም ጋር የተሰቀሉት ይነቅፉት ነበር

33 ስድስት ሰዓትም በሆነ ጊዜእስከ ዘጠኝ ሰዓት በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ

34 በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስኤሎሄኤሎሄላማ ሰበቅታኒ ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸትርጓሜውም አምላኬአምላኬለምን ተውኸኝ ? ማለት ነው

35 በዚያም ከቆሙት ሰዎች ሰምተውእነሆኤልያስን ይጠራል አሉ

36 አንዱም ሮጦ ሆምጣጤ በሰፍነግ ሞላ በመቃም አድርጎተዉኤልያስ ሊያወርደው ይመጣ እንደ ሆነ እንይ እያለ አጠጣው

37 ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኸ ነፍሱንም ሰጠ

38 የቤተ መቅደስም መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ

39 በዚያም በአንጻሩ የቆመ የመቶ አለቃ እንደዚህ ጮኾ ነፍሱን እንደ ሰጠ ባየ ጊዜይህ ሰው በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ አለ

40-41 ሴቶችም ደግሞ በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበርከእነርሱም በገሊላ ሳለ ይከተሉትና ያገለግሉት የነበሩ መግደላዊት ማርያም የታናሹ ያዕቆብና የዮሳም እናት ማርያም ሰሎሜም ነበሩከእርሱም ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የወጡ ሌሎች ብዙዎች ሴቶች ነበሩ

42 አሁንም በመሸ ጊዜ የሰንበት ዋዜማ የሆነ የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረየከበረ አማካሪ የሆነ የአርማትያስ ዮሴፍ መጣ

43 እርሱም ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበርደፍሮም ወደ ጲላጦስ ገባና የኢየሱስን ሥጋ ለመነው

44 ጲላጦስም አሁኑን እንዴት ሞተ ብሎ ተደነቀየመቶ አለቃውንም ጠርቶ ከሞተ ቆይቶአልን ? ብሎ ጠየቀው

45 ከመቶ አለቃውም ተረድቶ በድኑን ለዮሴፍ ሰጠው

46 በፍታም ገዝቶ አውርዶም በበፍታ ከፈነው ከዓለትም በተወቀረ መቃብር አኖረውበመቃብሩ ደጃፍም ድንጋይ አንከባለለ

47 መግደላዊትም ማርያም የዮሳም እናት ማርያም ወዴት እንዳኖሩት ይመለከቱ ነበር

16

1 ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቱ ገዙ

2 ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን እጅግ በማለዳ ፀሐይ ከወጣ በኋላ ወደ መቃብር መጡ

3 እርስ በርሳቸውምድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል ? ይባባሉ ነበር

4 ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርናአሻቅበውም አይተው ድንጋዩ ተንከባሎ እንደ ነበር ተመለከቱ

5 ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጎናጸፈ ጎልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ

6 እርሱ ግንአትደንግጡየተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁተነሥቶአልበዚህ የለምእነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ

7 ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስምወደ ገሊላ ይቀድማችኋልእንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው አላቸው

8 መንቀጥቀጥና መደንገጥ ይዞአቸው ነበርና ወጥተው ከመቃብር ሸሹይፈሩ ነበርና ለማንም አንዳች አልነገሩምእነርሱም ያዘዛቸውን ሁሉ ለጴጥሮስና ከእርሱ ጋር ላሉት በአጭሩ ተናገሩከዚህም በኋላ ኢየሱስ ራሱ ለዘላለም ድኅነት የሆነውን የማይለወጠውን ቅዱስ ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያው ድረስ በእጃቸው ላከው

9 ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜአስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ

10 እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው

11 እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደ ታያት ሲሰሙ አላመኑም

12 ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ በመንገድ በሌላ መልክ ተገለጠ

13 እነርሱም ሄደው ለሌሎቹ አወሩእነዚያንም ደግሞ አላመኑአቸውም

14 ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ተገለጠተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ

15 እንዲህም አላቸውወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ

16 ያመነ የተጠመቀም ይድናልያላመነ ግን ይፈረድበታል

17 ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋልበስሜ አጋንንትን ያወጣሉበአዲስ ቋንቋ ይናገራሉእባቦችን ይይዛሉ

18 የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውምእጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ

19 ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ

20 እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበርበሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር